ስምምነቶች እና መመሪያዎች

የአገልግሎት ስምምነት

መላቶፕን ለመጠቀም በሚከተሉት የአገልግሎት ሁኔታዎች መስማማት ይኖርብዎታል።

መላቶፕ ምንድን ነው?

መላቶፕ የተላያዩ አቃዎችን በ Online በማስተዋወቅ እና በመሸጥ ክፍያ የሚያገኙበት ድረገጽ (Affiliate Network) ነው።

ከተጠቃሚዎች የሚጠበቀው፦

በመላቶፕ የምዝገባ ሂደት ላይ የሚሰጡት መረጃ የእውነት፣ ትክክለኛ እና ሙሉ መሆን አለበት። መላቶፕ የመገልገያ አካውንቶን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ ወይም አገልግሎቱን የማቋረጥ ሙሉ መብት ያለው ሲሆን ይህም የሚሆነው አጠራጣሪ አጠቃቀሞች ሲስተዋሉ ነው።

የአካውንት ይለፍ ቃል እና ደህንነት፦

የምዝገባ ሂደቱን ሲያጠናቅቁ የይለፍ ቃል እና የመዝገብ መለያ ይኖርዎታል። የይለፍ ቃልዎን እንዲሁም አካውንትዎ ጋር ተያያዥ የሆኑ መረጃዎች ሚስጥራዊነት መጠበቅ የእርስዎ ሀላፊነት ነው። የይለፍ ቃልዎ Encrypt ሆኖ ስለሚቀመጥ ለመረጃ ጠለፋ አይጋለጡም። በተጨማሪም በይለፍ ቃልዎና አካውንትዎ ለሚካሄዱ ማናቸውም ተግባራት ሀላፊነት እንደሚወስዱ ይስማማሉ። እንዲሁም የይለፍ ቃልዎና የመለያ ስምዎ ያለእርስዎ ፍቃድ በሌላ አካል ጥቅም ላይ ከዋለ ወይም ሌላ የደህንነት ጥሰትም ካጋጠምዎ ለመላቶፕ ማሳወቅ ይኖርብወታል። ሆኖም መላቶፕ ለሚደርስብዎት ምንም አይነት ጉዳት ሀላፊነት አይወስድም። መላቶፕ የአካውንት ሽያጭን እና ለሌላ ሰው አካውንት አሳልፎ መስጠትን ይከለክላል።

የመላቶፕ ህግና ደንቦች

  • ማንኛውም የማጭበርበር ተግባራትን ካከናወኑ አካውንትዎ ይታገዳል።
  • የሚሸጠውን እቃ የማይወክል መግለጫ ምስል በመጨመር ለመሸጥ ከሞከሩ አካውንትዎ ይታገዳል።
  • በጊዜያዊነት የታገዱ አካውንትዎች በድጋሜ ለማስከፈት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ። ከአንድ ሳምንት ቡሀላ ግን አካውንቱ በቋሚነት የሚዘጋ ሲሆን ከዚያ በኋላ የሚመጡ ጥያቄዎች አይስተናገዱም።
  • የመላቶፕን መልካም ስምና ቀና ሀሳብ የሚያጎድፉ ማናቸውም ተግባራት ለአካውንት እገዳ ይዳርጋሉ።

ገቢና ክፍያ

በመላቶፕ ለሚደረግልዎ የገቢ ክፍያ የሚያስፈልጉ መርጃዎችን ለማሳወቅ ተስማምተዋል። ክፍያውን የመፈፀም ስልጣን ያለው መላቶፕ ብቻ ነው። ሁሉም የተጠቀሱት ክፍያዎች በኢትዮጵያ ብር ናቸው።